"ለሰው ሳይሆን ለጌታ እንደምትገዙ የምታደርጉትን ሁሉ በትጋት አድርጉት።" (ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3:23)

ወደ ቅዱስ አማኑኤል የአገልጋዮች መድረክ በሰላም መጡ። በዚህ ማህበረሰብ ውስጥ አገልግሎት ተግባር ብቻ ሳይሆን ቅዱስ መስዋዕትነት ነው። በቤተክርስቲያን ቅጥር ውስጥም ሆነ በስታዲየም ስራዎች፣ እያንዳንዱ እጅ የእግዚአብሔርን ፍቅር ለዓለም የሚያሳይ መሳሪያ ነው።

"And whatever you do, do it heartily, as to the Lord and not to men." (Colossians 3:23)

Welcome to the St. Amanuel Volunteer Hub. In this community, service is more than a task; it is a holy offering. Whether within the church walls or out in the mission fields of our city, every hand is an instrument of God's love.

የቦልቲሞር ታሪካችን | Our Baltimore Story

Where Faith Met the Field.

ባለፉት ሁለት ዓመታት የእግዚአብሔር ጸጋ በቤተክርስቲያናችን ግቢ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በቦልቲሞር ስታዲየምም ሲገለጥ አይተናል። ይህ ልዩ ተልዕኮ ማህበረሰባችንን በአዲስ መንፈስ ያገናኘበትና እውነተኛ የአገልግሎት ትርጉም የተገለጠበት ነበር።

የሚከተሉት ታሪኮች በዚህ ጉዞ ውስጥ የነበሩ አገልጋዮቻችን ምስክርነቶች ናቸው።

Over the last two years, we witnessed God’s grace move beyond our church walls and into the M&T Bank Stadium. This mission became a defining chapter for our community—a place where labor became worship. The stories below are the personal testimonies of those who led the way.